top of page
Search
  • negusbeer

Negus Brewing Company releases a new style of beer made with Teff grown in the US.

ንጉስ ቢራ ኩባንያ በአሜሪካ ከተመረተ ጤፍ የተዘጋጀ የጤፍ ቢራ አቀረበ


በላቀ ሁኔታ ተመራጭ የሆነው ንጉስ ቢራ በገበያ ላይ በአጭር ጊዜ ተወዳጅ ሆኖ መገኘቱን በማየት በአሜሪካ  ከሚመረት ጤፍ የተዘጋጀ በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ የጤፍ ቢራ ለገበያ የሚቀርብ ሲሆን በቅርቡ በDC, VA, NY, NC እና በሌሎች ብዙ እስቴቶች ይሰራጫል፡፡

ንጉስ ፐሬሚየም ክራፍት ላጋር የተባለው ቢራ የመጀመሪያ አምራች የሆነው የንጉስ ቢራ ኩባንያ ዛሬ /እ.ኤ.አ.መስከረም 30 ቀን 2019 ዓ.ም በኩባንያው ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ  አዲስ ጤፍ አምበር ኤል  በሚል መጠሪያ የተሰየመ በአሜሪካ ከሚመረት ጤፍ የተዘጋጀ ማራኪ የሆነ ልዩ ቢራ ማቅረቡን ያሳውቃል፡፡

እ.ኤ.አ. በ2016 የተቋቋመው ንጉሥ ቢራ ኩባንያ የመጀሪያውን ፐሪምየም ላጋር ቢራ ለገበያ በማቅረብና የስርጭቱን አውታሮች በ DC, MD, VA, NY በማስፋፋት ምርቱን የማስተዋወቅ ሥራ አስደናቂ ውጤት አምጥቶለታል፡፡የገበያ አድማሱንም በNC, GA, MN ለማስፋትየጀመረውን ዕቅድ አጠናቋል፡፡

ንጉስ ቢራ ኩባንያ ከዓመታት ምርምርና ሙከራ በኋላ በሳይዙ ትንሽ ሆኖ ነገር ግን በምግብ ንጥረ ነገር ይዘቱ በዓለም ካሉ ምርቶች የተሻለ ሆኖ ከተገኘው ጤፍ በዓይነቱ ልዩ የሆነ ቢራ ለማምረት በቅቷል፡፡ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያና በኤርትራ ብቻ በዋነኛነት በእንጀራ መልክ ለምግብነት የሚውል ቢሆንም ጤፍ ከግሉቲን ነፃ በመሆኑ፣ በውስጡም የተለያዩ የምግብ ንጥረ ነገሮች ያሉትና  በተለያዩ የምግብ አዘገጃጀቶች ምቹ በመሆኑ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ ታዋቂነትን ያተረፈ ከመሆኑም በላይ  የወደፊቱ የዓለም ዓይነተኛ ምግብ (The next super food) የሚል ዕውቅና ተችሮታል፡፡ እንዳጋጣሚ ሆኖ በጤፍ ላይ በቂ ክትትል ባለመደረጉ በቅርቡ በዓለም ሁሉ መገጋገሪያ የሆነው አንድ የዴች ካምፓኒ የጤፍ ብቸኛ ባለቤት እንደሆነ በማድረግ እውቅና  ለማግኘት ሙከራ ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ጉዳዩን ለፍርድ ቤት በማቅረብ በጥንካሬ በመከራከሩ የካምፓኒው ሙከራ ሊከሽፍ ችሏል፡፡ ምንም እንኳ ኢትዮጵያ በክርክር የረታች ቢሆንም የጤፋችንን የባለቤትነት መብት ማስከበር፣  ለዓለም ማስተዋወቅና አጠቃቀሙን ማስፋትና ማሰራጨት የእኛ የኢትዮጵያውያን መብትና ግደታ ነው፡፡ ብዙ ትልልቅ ካምፓኒዎች ከግሉትን ነፃ የሆነ ፓስታ፣ ዳቦ፣ ኬክና የመሳሰሉትን ከጤፍ በማዘጋጀት ከፍተኛ ገቢ እያገኙበት ሲሆን እኛ ኢትዮጵያውያን ግን የጤፍን አጠቃቀም ለማስፋፋት አሁን ድረስ ጥረት ስናደርግ አይታይም፡፡በመሆኑም የንጉሥ ቢራ ኩባንያ ጤፍን ለጥሬ ዕቃነት በመጠቀም እና ሌሎች የጤፍ አጠቃቀሞችን በመስፋት ዓለም ዓቀፍ እውቅና አንዲኖረው ለማድረግ በመሥራት ላይ ይገኛል፡፡

ጤፍን ለቢራ ጥሬ ዕቃነት በስፋት ለመጠቀም  አቅርቦቱን ከእናት ሀገር ባለማድረግ በሀገራችን የጤፍ እጥረት እንደይፈጠር ኩባንያችን ጥሬ ዕቃውን ከአሜሪካ ጤፍ አምራች ገበሬዎች ብቻ የሚገዛ ሲሆን በቀጣይ በአሜሪካ የራሱ የጤፍ የእርሻ መሬት እንዲኖረው ለማድረግ አቅዷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በሀገራችን የጤፍ እጥረትን በዘላቀነት ለማስወገድ እንዲቻል የምርቱን መጠን ከፍ ለማድረግ በሀገራችን በጤፍ ላይ የእርሻ ምርምሮችን ለማጠናከር ኩባናያችን ከሚያገኘው ትርፍ ላይ ድጐማ ለማድረግ ዕቅድ ይዟል፡፡ የጤፍን ጠቀሜታ ከማስፋፋት አልፎም የንጉሥ ቢራ ኩባንያ  ጠላ፣  ጠጅ፣ ከአልክሆል ነፃ  ቢራ አና ሌሎችን የኢትዮጵያን ባህላዊ መጠጦች የሚያስተዋውቁና ገጵታዋን የሚያሰፉ የመጠጥ ዓይነቶችን ለማቅረብ የምርምርና የሙከራ ሥራውን ያጠናቀቀ ሲሆን ምርቶቹን በቅርብ ጊዜ ለገበያ ያቀርባል፡፡

በዚሁ የጤፍ ቢራ አቅርቦት ማስታወቂያ ኩባንያው ካፒታሉን ለማሳደግ በውጭ ሀገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያንና በሀገር ውስጥ የኩባንያውን ዓላማ የሚደግፉ ሁሉ የአክስዮን ግዥ እንዲፈጽሙ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ባለበት ጊዜ መሆኑ ይህን ተልዕኮ ለማሳካት እገዛ የሚያደርግ መልካም አጋጣሚ ሲሆን በሽያጭ አክስዮን ዙሪያ ሰፋ ያለ መረጃ በዌብ ሳይታችን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የምናቀርብ መሆኑን ከወዲሁ እየገለጽን እንድትከታተሉ በትህትና እናሳውቃለን፡፡

ንጉስ ቢራ ኩባንያ

ቨርጂኒያ አሜሪካ

25 views0 comments
bottom of page